- ቁርኣን የዘላቂ ደስታ ጎዳና -

- ቁርኣን የዘላቂ ደስታ ጎዳና -

አንዳንዶች ስለ ቁርኣን ሰዎች ማንነት ይጠይቁሃልና እነሱ በፀጋ ውስጥ ነው ያሉት በላቸው። ምክንያቱም እነሱ ቁርኣንን በቃላቸው በመሸምደድ፣ መላልሰው በማንበብና በማስተንተን የተጠመዱ ናቸውና።

🍃ስለዚህ እነሱ በጌታቸው ንግግር እያዜሙ በዱንያ ጀነት ውስጥ ፀጋውን በመቋደስ ላይ ነው ያሉት። ልባቸውም ጌታቸውን በማውሳት የሰፋ ነው።

ጌታዬ ሆይ ፀጋህንና ደስታን ጨምርላቸው። የመጨረሻው ግባቸው ያንተን ፍቅርና ውዴታ ማግኘት ብሎም በመጨረሻዋ ዓለም
”اقرأ وارتق ورتل فإن منزلتك عند آخر آية تقرؤها “
“አንብብ፣ ከፍ በልበት፣ ቃል በቃልም በርጋታ አነብንበው። ያንተ ቦታ መጨረሻ ላይ የምታነብባት አንቀፅ ዘንድ ነው።” በሚለው የብስራት ቃል ለስኬት መድረስ ነው።

የቁርኣን ሰዎች ሆይ ምንኛ ታድላችኋል? አላህ ያፅናችሁ። እኛንም ይወፍቀን።

https://t.me/almunirquranicacademy
በአል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ የሚቀርቡ የተለያዩ የቁርኣን ንባብ እና የቁርኣን ንባብ ህግጋቶች መማማሪያና መጠያየቂያ official ግሩፕ ነው:: ጆይን በማለት የትምህርቱ ተካፋይ ይሁኑ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *