- ቁርኣን የዘላቂ ደስታ ጎዳና -

- ቁርኣን የዘላቂ ደስታ ጎዳና -

Al Munir Qur’anic Academy - አል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ
አል ሙኒር የቁርኣን አካዳሚ በሰላም ሚኒስቴር ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ሀገር አቀፍ የቁርኣን ማዕከል ነው። በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በአዳሪና ተመላላሽ መርሀ ግብር እንድሁም በonline (የመስመር ላይ) አማራጭን ዘርግቶ ትምርቱን እየሰጠ የሚገኝ ቁርኣን ማዕከል ነው። የማስተማር ሂደቱን በሀራችን ዙሪያ በሚገኙ ብቁ እና በተረጋገጡ የቁርአን ሑፋዞች የሚሰጥ ሲሆን ፤ የቀጥታ (online) ትምህርቶች የበይነመረብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቀላል፣ ምቹና ዘመናዊ በሆኑ የማስተማሪያ መንገዶች እያስተማረ የሚገኝ ማዕከል ነው።

የአል ሙኒር አካዳሚ ራዕይ

ምቹና ውጤታማ የሆነ ስልትን በመጠቀም ቁርአንን መሐፈዝ ወይም በቃል መሸምደድ እንዲችል ማድረግና ጠንካራ እንድሁም በስነም ምግባር የታነፁ ቁርኣን ሓፊዞችን ማፍራት።

የአል ሙኒር አካዳሚ አላማ

  1. የተቀናጀና ስኬታማ የሆነን ስልት በመጠቀም ፤ ቁርኣንን በትክክል እና በተሳካ መልኩ ለማንበብም ሆነ ለመሐፈዝ ለሚፈልጉ ሰዎች ምቹ መንገድን መፍጠር።
  2. ቁርኣንን ለመሐፈዝ የሚከለክሉና እንቅፋት የሚሆኑ መሰናክሎችን አቅማችን በፈቀደ መልኩ በማስወገድ መንገዱን ማግራት።
  3. የሀገራችንን ሙስሊም ማህበረሰብ የጌታቸውን ቃል አጥብቀው ወደ መያዝ እንዲመለሱ ምክንያት መሆንና በዚህም መልካም ነገርን ሁሉ እንዲያገኙ ብሎም ከመጥፎ እንዲከለከሉ ሰበብ መሆን።
  4. በሀገራችን ለሚገኙ ሐፊዞች ቁርኣንን መሐፈዝና ማ’ሰማት ብቻ ሳይሆን ከሐፈዙም በኋላ በትክክል የሐፈዙትን በልባቸው ማስረፅና ማፅናት የሚችሉበትን ስልት በማዘጋጀት ማስተማር ፣ ኮርስ መስጠት።
  5. ቁርኣንን በበለጠ ለመረዳት በሚቀል መልኩ አናቅፆቹን በመከፋፈል እያንዳንዱ ተሳታፊ የአላህን ቃል በተገቢው መልኩ ማስተንተን እንዲችል ማገዝ።
  6. በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ከግል ችሎታና የአቅም ልዩነቶች ጋር የሚጣጣሙ ፕሮግራሞችንና የአቀራረብ ስልቶችን አሟልቶ ማቅረብ።
  7. በፕሮግራሙ ተሳታፊ የሆነ ሰው የሐፈዘውን ቁርኣን ክትትል የሚያደርግለት ሰው ሳያስፈልገው በደንብ ለመሐፈዝና ትክክለኛ በሆነ መልኩ ለማንበብ የሚያስችለውን ምርጥ ዘዴ ማመቻቸት። ወዘተ ናቸው

 

 

 

የቁርኣን አስተማሪዎች(ኡስታዞች)

አባልት ኡስታዞች
 
 

ኡስታዝ ጀማል አህመድ

ስራ አስኪያጅ

ኡስታዝ አንዋር ሰይድ

ተቆጣጣሪ

ኡስታዝ ሙሀመድ አህመድ

ኡስታዝ

ኡስታዝ አህመድ

ኡስታዝ

ተማሪዎች
0
የዓመታት ልምድ
0